ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ለሲዳማ ቡና የቡድን አባላት ሽልማት ተበረከተ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ለሲዳማ ቡና የቡድን አባላት ሽልማት ተበረከተ !
ለሲዳማ ቡና የቡድን አባላት ሽልማት ተበረከተ !

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡና አባላት ሽልማት እንደተበረከተላቸው ተገልጿል።

ሲዳማ ቡና ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ድሉን ከደጋፊው ጋር በድምቀት አክብሯል።

የሲዳማ ክልል መንግሥት በበኩሉ ለቡድኑ ይፋዊ የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር ምሽት ላይ አዘጋጅቷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የክልሉ መንግሥት :-

- ለሲዳማ ቡና የቡድን አባላት 1️⃣ ሚልዮን ብር እና 2️⃣0️⃣0️⃣ ካሬ መሬት ሸልሟል።

- በዓመቱ ኢጋማሽ ቡድኑን የተቀላቀሉ እንዲሁም ቀሪ ተጫዋቾች 2️⃣0️⃣0️⃣ ካሬ ሜትር

- ለአመታት ክለቡን በታማኝነት ሲደግፍ ለነበረው ኢያሱ ሱዳ 2️⃣0️⃣0️⃣ ካሬ ሜትር ቦታ ተበርክቷል።

- ለቀድሞ ለክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሳሳሞ 2️⃣0️⃣0️⃣ ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።

- ለሲዳማ ቡና ከ 20ዓመት በታት ተጫዋቾች በድምሩ 6️⃣ ሚልዮን ብር

- ለሲዳማ ቡና ከ 20ዓመት በታች ዋና አሰልጣኝ አምሀ ዘውዱ 2️⃣0️⃣0️⃣ ካሬ መሬት ሸልሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች