ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሊቨርፑል በዝውውሩ ቅድሚያ ለማን ሰጠ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሊቨርፑል በዝውውሩ ቅድሚያ ለማን ሰጠ ?
ሊቨርፑል በዝውውሩ ቅድሚያ ለማን ሰጠ ?

በአዲስ አሰልጣኝ የሚመራው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኮከባቸውን ሞሀመድ ሳላህ ተተኪ ማግኘት ተቀዳሚ ስራቸው አድርገዋል።

ሊቨርፑሎች በስፋት ወደ ገበያው ለመውጣት የአለም ዋንጫውን መጠናቀቅ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

የፊት መስመሩን ማጠናከር ተቀዳሚ ስራቸውን ሲሆን በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ሁጎ ኢክቲኬ የማገገሚያ ልምምዶችን መስራት መጀመሩ ተዘግቧል።

ክለቡ በፊት መስመር ቦታ ላይ የፒኤስጂውን ብራድሊ ባርኮላ የማስፈረም ፍላጎት ሲኖራቸው በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑም ተገልጿል።

በተጨማሪም :-

- ያንኩባ ሚንቴ ( ብራይተን )
- ሰይድ ኤል ማላ ( ኮሎኝ )
- ማቲያስ ፈርናንዴዝ ፓርዶ ( ሊል ) በአማራጭነት በክለቡ የዝውውር እቅድ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ አዲስ ተጫዋች ከማስፈረም ባለፈ ክለቡን እንዲለቁ የሚፈልጓቸው ተጫዋቾች ሲኖሩ :-

- ከርትስ ጆንስ
- ፍሬደሪኮ ኬይዛ
- ሀርቪ ኢልዮት በክለቡ የመቆየት እድላቸው አጠራጣሪ ሆኖ ይገኛል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች