ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ሊዮኔል ሜሲ ነገ ያገባል “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ሊዮኔል ሜሲ ነገ ያገባል “
“ ሊዮኔል ሜሲ ነገ ያገባል “

“ ለአሰልጣኛችን ማሸነፍ እንፈልግ ነበር “

“ ኮከብ ግብ አግቢ ሳልሆን ፍፃሜ መጫወትን እመርጣለሁ “

የአለም ዋንጫውን የኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ አሰልጣኝ ዲድዬ ዴሾን አመግኗል።

ምባፔ “ ለፈረንሳይ ላደረገው ነገር ሁሉ አመሰግነዋለሁ “ ያለ ሲሆን የምሽቱ ጨዋታ ውጤት “ ታሪካዊነቱን አይሽረውም “ ሲል ገልጿል።

አክሎም “ ለአሰልጣኛችን ማሸነፍ ፈልገን ነበር ፣ ነገር ግን በመጀመሪያው አጋማሽ ያሳየነው እንቅስቃሴ እንደከዳነው ያህል ተሰምቶኛል “ ብሏል።

ምባፔ ስለ ኮከብ ግብ አግቢነቱ ሲጠየቅ “ ሊዮኔል ሜሲ ነገ ያገባል “ ያለ ሲሆን “ ምክንያቱም እሱ ሁሌም ጎል ያገባል ፣ ሪከርዶች ላይ ፍላጎት የለኝም “ ሲል ተናግሯል።

“ ኮከብ ግብ አግቢ ሳልሆን ቀርቼ የነገውን ፍፃሜ መጫወትን እመርጣለሁ “

ኪሊያን ምባፔ

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች