ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማንችስተር ሲቲ ምን ያስፈርማል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማንችስተር ሲቲ ምን ያስፈርማል ?
ማንችስተር ሲቲ ምን ያስፈርማል ?

ከሮድሪ እና ቲጃኒ ሬንደርስ ጋር ለመለያየት የተቃረበው ማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳውን ለማጠናከር አቅዷል።

ማንችስተር ሲቲዎች የሊሉን አማካይ አዩብ ቦኣዲ ለማስፈረም እየተቃረቡ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በተጨማሪም ኢንዞ ፈርናንዴዝን የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው እና ተስፋ እንዳልቆረጡ ተዘግቧል።

ክለቡ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርግ ሲገለፅ ይሁን እንጂ 120 ሚልዮን ፓውንድ የመክፈል ሀሳብ የለውም ተብሏል።

ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ክለቡን በሚለቁ ተጨዋቾች ቦታ አዲስ ተጨዋች ማስፈረም እንዳሰበ ተነግሯል።

ይህም ማለት ሳቪንሆ ወደ ቶተንሀም የሚያደርገውን ዝውውር ካጠናቀቀ የክንፍ ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሮድሪ ፣ ሳቪንሆ ፣ ሬንደርስ እና ጃክ ግሪሊሽ በዚህ ክረምት ክለቡን የሚለቁ እና ሊለቁ የሚችሉ ተጨዋቾች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች