ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሜሪኖ ለስፔን በቋሚ አሰላለፍ መጀመር አለበት ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሜሪኖ ለስፔን በቋሚ አሰላለፍ መጀመር አለበት ?
ሜሪኖ ለስፔን በቋሚ አሰላለፍ መጀመር አለበት ?

ሚኬል ሜሪኖ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በአለም ዋንጫው ሀገሩን አሸናፊ ሲያደርግ አዲሱ የቡድኑ ኮከብ እና ጀግና ሆኖ ብቅ ብሏል።

ቡድኑ በጥሎ ማለፉ ከ ፖርቹጋል እና ቤልጅዬም ጋር ባደረገው ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት የማሸነፊያ ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወሳል።

በቋሚ አሰላለፍ መጀመር የሚያስችለውን አቋም እንዳሳየ የሚነገርለት ሜሪኖን ለማሰለፍ አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ከመደበኛ አሰላለፋቸው አንድ ተጫዋችን ለመቀነስ ይገደዳሉ።

አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ በቋሚ አሰላለፍ ምርጫቸው ላይ ያልተጠበቁ ውሳኔዎችን ባለፉት ጨዋታዎች ሲወስኑ ተስተውለዋል።

ቡድኑ ከቤልጂየም ጋር ባደረገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ፔድሪን በ ፋቢያን ሩይዝ በመተካት ውሳኔዎችን ለማድረግ ወደ ኃላ እንደማይሉ አሳይተዋል።

አሰልጣኙ የአርሰናሉን አማካይ ሚኬል ሜሪኖን ለመጠቀም ካሰቡ በዳኒ ኦልሞ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ቦታ ላይ ወይስ በሀሰተኛ 9️⃣ ቁጥር በሚኬል ኦያርዛባል ቦታ ላይ የሚለው ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች