ሮናልዲንሆ ጎቾ ለጣልያን ክለብ ፈረመ !

ሮናልዲንሆ ጎቾ ለጣልያን ክለብ ፈረመ !
የቀድሞ የብራዚል ተጨዋች ሮናልዲንሆ ጫማ ከሰቀለ አስራ አንድ አመታት በኋላ ወደ እግር ኳስ ተመልሷል።
ሮናልዲንሆ ጎቾ በጣሊያን ሶስተኛ ዲቪዚዮን ለሚሳተፈው ራቬና እግር ኳስ ክለብ ፈርሟል።
በዛሬው ዕለት ወደ ጣልያን ያመራው ሮናልዲንሆ ከክለቡ ባለቤቶች ውስጥ አንዱ መሆኑም ተገልጿል።
ሮናልዲንሆ ዛሬ የክለቡ አዲስ ፈራሚ ሆኖ የሚተዋወቅ ሲሆን ስድስት ሺ አካባቢ ደጋፊዎች ይጠበቃሉ።
በቡድኑ ቀጣይ ጨዋታ ዝግጁ ስለመሆኑ ያልተነገረ ሲሆን አላማው የእግርኳስ ህይወቱ የመጨረሻ ጎል ማስቆጠር መሆኑ ተነግሯል።
የ 46ዓመቱ ሮናልዲንሆ ለመጨረሻ ጊዜ ሜዳ ላይ የታየው 2015 በፍሉሚኔንስ ማልያ ነበር።
@tikvahethsport @YisakAH