“ በቀኝ የተገዛ ካሜሮናዊ “ የፓራጓይ ሴናተር

“ በቀኝ የተገዛ ካሜሮናዊ “ የፓራጓይ ሴናተር
“ ጉዳዪን ወደ ህግ ወስደነዋል “ የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
“ የፓራጓይን ህዝብ አትወክዪም “ ኪሊያን ምባፔ
የፓራጓይ ሴናተር ሴሌስቴ አማሪላ ኪሊያን ምባፔ ላይ ያስተላለፉት የዘረኝነት መልዕክት“ በቀኝ የተገዛ ካሜሮናዊ “ ማለታቸው ቁጣን ቀስቅሷል።
ኪሊያን ምባፔ የሴናተሯን ድርጊት ተከትሎ "አጸያፊ እና ዘረኛ" ሲል ገልጿቸዋል።
የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አምበላቸው ላይ የደረሰውን የስም ማጥፋት ተከትሎ ጉዳዩን ወደ ሚመለከተው የህግ አካል መወሰዱን አሳውቋል።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት “ ሁሉንም ድጋፌን ታገኛለህ “ ሲሉ ድጋፋቸውን ገልፀውለታል።
የፓራጓይ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር መንግስትን ወክሎ የሴናተሯ ጉዳይ ውስጥ እንደሌለበት በ “ X “ የማህበራዊ ትስስር ገፅ አጋርቷል።
የ 61ዓመቷ ጠበቃ እና የፓርቲ አባል አማሪላ ኪሊያን ምባፔን ለመተቸት የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ስትጠቀም ነበር።
ከፓራጓይ እና ፈረንሳይ ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ ሴናተሯ ምባፔን “ አስቀያሚ “ ሲሉ “ ሙሉ ጨዋታውን ተረብሾ እና ፈርቶ ነው የጨረሰው “ ብላዋል።
ኪሊያን ምባፔ በበኩሉ “ የፓራጓይን ህዝብ አትወክዪም ፣ ባስተላለፍሽው የዘረኝነት መልዕክት አለም የፓራጓይን አስደናቂ የአለም ዋንጫ ጉዞ ረስቷል “ ብሏል።
ኪሊያን ምባፔ ፓራጓይ እና ፈረንሳይ ባደረጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብቸኛውን የማሸነፊያ ጎል ያስቆጠረው ተጫዋች ነበር።
@tikvahethsport @kidusyoftahe