“ ባሕር ዳር ላይ ብዙ የሽንፈት ታሪክ የለንም ” ከነአን ማርክነህ

የዋልያዎቹ የፊት መስመር ተሰላፊ ከነአን ማርክነህ ለነገው ጨዋታ ጥሩ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጿል።
“ ጥሩ ዝግጅት አድርገናል በጥሩ መንፈስ ላይም እንገኛለን “ ሲል ከነአን ማርክነህ ስለ ቡድኑ ዝግጁነት ተናግሯል።
“ በባሕር ዳር ስታዲየም ብዙ የሽንፈት ታሪክ የለንም ” ያለው ከነአን “ ነገም በዚህ መንፈስ እንጫወታለን “ ሲል ገልጿል።
ቡድኑ በሱዳን ጨዋታ የነበሩ ስህተቶችን በማረም “ የተሻለ ስነልቦና ይዘን እንቀርባለን ” ሲልም ተናግሯል።
ለህዝቡ መልዕክት ያስተላለፈው ከነአን ማርክነህ “ የባሕር ዳር ሕዝብ ኳስ ወዳድ ነው ነገም እንደ ቀደመው ጊዜ መጥታችሁ ድጋፋችሁን ስጡን “ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe