ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ባሕር ዳር ስታዲየም ፍቃድ አገኘ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ባሕር ዳር ስታዲየም ፍቃድ አገኘ !
ባሕር ዳር ስታዲየም ፍቃድ አገኘ !

የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ካፍ ባሕር ዳር ስታዲየም የጥራት መስፈርቱን ባለሟሟላቱ ለአመታት አግዶት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይህንንም ተከትሎ ስታዲየሙ መስፈርቱን እንዲያሟላ የማሻሻያ ግንባታ ሲደረግለት መቆየቱ አይዘነጋም።

አሁን ላይ ካፍ ለስታዲየሙ ጊዜያዊ ፍቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን በስታዲየሙ እንዲያደርግ ፍቃድ መስጠቱን አክሎ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

የአማራ ክልል ባህል ፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ በበኩላቸው በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ ስታዲየሙ ለአለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ ሆኗል " ብለዋል።

በቀጣይ ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከ ሴኔጋል ጋር የሚያደርጉት የማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታ በስታዲየሙ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች