ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ተጋጣሚያችን ሞሮኮ እንጂ ዳኛው አይደለም ” ዲዲዬ ዴሾ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ተጋጣሚያችን ሞሮኮ እንጂ ዳኛው አይደለም ” ዲዲዬ ዴሾ
“ ተጋጣሚያችን ሞሮኮ እንጂ ዳኛው አይደለም ” ዲዲዬ ዴሾ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ከነገው የሞሮኮ ጨዋታ በፊት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ሞሮኮ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾች መያዟን ያነሱት አሰልጣኙ “ ትልቅ ጥረት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

“ እነሱ የእኛን ተጨዋቾች በደንብ ያውቋቸዋል ነገርግን የእኛም ተጨዋቾች እነሱን በደንብ ያውቋቸዋል “ ሲሉ ዲዲዬ ዴሾ ተናግረዋል።

ሁሉም የጨዋታው ዳኞች አርጀንቲናዊ ስለመሆናቸው የተጠየቁት አሰልጣኙ “ ተጋጣሚያችን ሞሮኮ ነች ዳኛውን ተጋጣሚ አድርገን አናስብም ” ብለዋል።

አክለውም “ ሁልጊዜ ከግለሰብ ጥንካሬ ይልቅ የቡድን ጥንካሬ የተሻለ እንደሆነ አምናለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች