ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ትልቅ ነገር የማሳካት አቅም አለን ” ማይክል ካሪክ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ትልቅ ነገር የማሳካት አቅም አለን ” ማይክል ካሪክ
“ ትልቅ ነገር የማሳካት አቅም አለን ” ማይክል ካሪክ

“ የሀል ሲቲ ጨዋታ በጣም ከባድ ነው ”

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ አመቱን ለመጀመሪያ ጓጉቻለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ያለፈው አመት ውጤት በራስ መተማመን እንደጨመርላቸው የገለፁት ካሪክ “ አዲስ አመት እንደሆነም እናውቃለን ዝግጁ ነን “ ብለዋል።

አክለውም “ ትልቅ ነገር የማሳካት አቅም አለን ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ አንችልም ልል አልችልም " ሲሉ ገልጸዋል።

ስለ ሀል ሲቲ ጨዋታ ያነሱት ካሪክ “ ሰዎች እንደሚሉት በፍጹም ቀላል ጨዋታ አይደለም “ ብለዋል።

“ አዲስ ያደገ ቡድንን በሜዳው መግጠም በጣም አስቸጋሪ ነው ካለኝ ልምድ አንፃር ቅድሜ ምን እንደሚጠብቀን እረዳለሁ ” ሲሉ ካሪክ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች