ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ትኩረት የሳበው የጃፓን ተጨዋቾች ድርጊት !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ትኩረት የሳበው የጃፓን ተጨዋቾች ድርጊት !
ትኩረት የሳበው የጃፓን ተጨዋቾች ድርጊት !

ከጃፓን ቁልፍ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ታኩሚ ሚናሚኖ በጉልበት ጉዳት ምክንያት ከአለም ዋንጫው ውጪ መሆኑ ይታወቃል።

የቀድሞ የቡድኑ አምበል ማያ ዮሺዳ በበኩሉ ከቡድኑ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ በዚህ አለም ዋንጫ አልተሳተፈም።

ይሁን እንጂ ሁለቱ ተጨዋቾች በዚህ አለም ዋንጫ ከሜዳ ውጪ ባላቸው ሀላፊነት ለብዙዎች አርኣያ መሆን ችለዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሞርያሱ ሁለቱ ተጨዋቾች በአለም ዋንጫው ወቅት ልዑክ ቡድኑን እንዲያግዙ ጋብዘዋቸው ነበር።

ታዲያ ተጨዋቾቹ ወጣት ተጨዋቾችን ከመምከር እና አሰልጣኝ አባላትን ከማገዝ ባሻገር ያደረጉት ነገር አድናቆት አስችሯቸዋል።

ሚናሚኖ እና ዮሺዳ መልበሻ ቤቱን እንደሚያዘጋጁ ፤ በልምምድ ወቅት ኳስ እንደሚሰበስቡ እና መገልገል ቁሳቁስ እንደሚያከፋፍሉ ተነግሯል።

በተጨማሪም የቡድን አጋሮቻቸውን የመጫወቻ ጫማዎች እንደሚያፀዱ ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ አምበሎች እና አሰልጣኝ በቡድኑ ትልቅ ታሪክ ያላቸው ተጨዋቾች ድርጊት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሞሪያሱ በሰጡት ቃል “ የእነሱ ድርጊት ማንም ከቡድኑ በላይ አለመሆኑን ያረጋገጠ ነው “ ሲሉ ገልፀውታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች