ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለመጠቀም እየሰራን ነው “ አቶ ኢሳያስ ጂራ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለመጠቀም እየሰራን ነው “ አቶ ኢሳያስ ጂራ
“ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለመጠቀም እየሰራን ነው “ አቶ ኢሳያስ ጂራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ አቶ ኢሳያስ ጂራ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አቶ ኢሳያስ ጂራ በቆይታቸው በቀጣይ ለመሥራት ስላቀዷቸው ሥራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአጭር ጊዜ እቅዳቸውን ያሳወቁት አቶ ኢሳያስ “ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችን ለመጠቀም ከመንግሥት ጋር እየሰራን ነው “ ብለዋል።

ብሔራዊ ቡድን እንደሚያጠናክሩ የገለፁት አቶ ኢሳያስ “ የአጭር እና ረጅም ጊዜ እቅድ ይዘን የምንሰራ ይሆናል “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አያይዘውም በቀጣይ " መሰረተ ልማት " ማሟላት ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ አቶ ኢሳያስ ጂራ ተናግረዋል።

እንደ ማሳያም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ ሱሉልታ ላይ ቴክኒካል ማዕከል ለመገንባት ማቀዱን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሱሉልታ ላይ አስር ሄክታር መሬት ቃል እንደገቡላቸው አቶ ኢሳያስ ጂራ ተናግረዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች