ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ቶተንሀም ወይስ አስቶን ቪላ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ቶተንሀም ወይስ አስቶን ቪላ ?
ቶተንሀም ወይስ አስቶን ቪላ ?

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የምሳ ሰዓት መርሐ ግብር አስቶን ቪላ እና ቶተንሀም ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ሁለቱ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ እያንዳንዳቸው አስር ተጨዋቾች ወደ ቡድናቸው መቀላቀል ችለዋል።

ያለፈውን አመት አስራ ሰባተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ቶተንሀም በዝውውር መስኮቱ ቡድኑን አጠናክሯል።

አስቶን ቪላ በበኩሉ ኮከቦቹን በሌሎች ክለቦች መቀማቱን ተከትሎ በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።

ይሁን እንጂ ሁለቱም ክለቦች ደካማ የተባለ የውድድር ዘመን ጅማሮ አድርገዋል።

ቶተንሀም እና አስቶን ቪላ ከመጀመሪያ አራት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ አልቻሉም።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ :-

- ቶተንሀም በ 2 ነጥብ 17ኛ
- አስቶን ቪላ በ 1 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች