ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ቼልሲ ስንት ተጨዋቾቹን ይሸጣል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ቼልሲ ስንት ተጨዋቾቹን ይሸጣል ?
ቼልሲ ስንት ተጨዋቾቹን ይሸጣል ?

ቼልሲ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ዣቢ አሎንሶ የ 24 ተጨዋቾች ስብስብ ይዘው ነበር።

አሰልጣኙ ከስብስባቸው ያስቀሯቸው በርካታ ተጨዋቾች ክለቡን የሚለቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ጉዳት ሳይገጥማቸው በቡድኑ ካልነበሩ ተጨዋቾች መካከል :-

- ኒኮላስ ጃክሰን
- ሊያም ዴላፕ
- ማይካሎ ሙድሪክ
- አዳራብዮ
- ማማዱ ሳር
- አንሴልሚኖ
- ማርክ ጉዩ እና አክሴል ዲሳሲ ይገኙበታል።

እነዚህ ተጨዋቾች በዚህ ክረምት ክለቡን በቋሚነት እና በውሰት የሚለቁ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቅዳሜ ከያዙት የ 24 ተጨዋቾች ስብስብ የተወሰኑት ይለቃሉ ተብሏል።

ቼልሲ ይህንን የሚያደርገው ተጨዋቾችን በመሸጥ ገንዘብ ለማሰባሰብ አልሞ እንዳልሆነ ተገልጿል።

ክለቡ በአውሮፓ የማይሳተፍ በመሆኑ በጨዋታ እጥረት የተበሳጩ ተጨዋቾች በቡድኑ እንዳይኖሩ ቡድኑን ለመመጠን አስቦ መሆኑ ተዘግቧል።

ቼልሲ በቀጣይ ትኩረቱ ተጨዋቾችን መሸጥ ላይ እንደሚሆን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች