ቼልሲ ስኬታማውን የቆመ ኳስ አሰልጣኝ ይቀጥር ይሆን ?

ቼልሲ ስኬታማውን የቆመ ኳስ አሰልጣኝ ይቀጥር ይሆን ?
የአስቶን ቪላ የቆመ ኳስ አሰልጣኝ ኦስቲን ማክፊ ክለቡን ከአምስት አመታት በኋላ እንደሚለቁ ተገልጿል።
አስቶን ቪላ አሰልጣኙን ሊያቆያቸው ጥረት ቢያደርግም አዲስ ነገር በመፈለግ ክለቡን ለመልቀቅ ወስነዋል ተብሏል።
የ 46ዓመቱን የቆመ ኳስ አሰልጣኝ ኦስቲን ማክፊ ቼልሲ ሊቀጥራቸው እንደሚፈልግ ተዘግቧል።
በተጨማሪም አንድ የፕሪሚየር ሊግ እና የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር አሰልጣኙ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል።
አሰልጣኙ በእንግሊዝ የሚቆዩ ከሆነ የሚቀላቀሉት ክለብ ቼልሲ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል።
አስቶን ቪላ ባለፈው የውድድር ዘመን በአሰልጣኙ ስር በአውሮፓ በቆመ ኳስ ከተካኑ ክለቦች መካከል አንዱ ሆኖ ነበር።
ክለቡ በውድድር አመቱ ከአርሰናል እኩል 29 የቆመ ኳስ ጎል በማስቆጠር ከአውሮፓ ቀዳሚው ክለብ ነበር።
@tikvahethsport @kidusyoftahe