ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ንግድ ባንክ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ንግድ ባንክ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ !
ንግድ ባንክ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴት ቡድን የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ሴካፋ ዞን ውድድሩን በድል ጀምሯል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከጅቡቲው ኡጄኮ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 11ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እሙሽ ዳንኤል አምስት ጎሎችን ማስቆጠር ችላለች።

ቀሪዎቹን የንግድ ባንክ ጎሎች እፀገነት ግርማ 2x ፣ ሊዲያ እያሱ 2x ፣ እፀገነት ግርማ  እና ታሪኳ ዴቢሶ አስቆጥረዋል።

እሙሽ ዳንኤል የውድድሩን ኮከብ ግብ አግቢነት ደረጃ በመምራት ላይ ትገኛለች።

ቡድኑ በመጀመሪያው አጋማሽ ስድስት በሁለተኛው አጋማሽ አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ንግድ ባንክ በቀጣይ ሰኞ ከ ዩጋንዳው ክለብ ኩዋምፔ ፖሊስ ጋር ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን የሚያሸንፍ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ያረጋግጣል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች