ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የብሬንፎርድ ስኬታማ ጉዞ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የብሬንፎርድ ስኬታማ ጉዞ !
የብሬንፎርድ ስኬታማ ጉዞ !

ብሬንትፎርድ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደጉ ወዲህ ከተጠበቀው በላይ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

በሊጉ ከቆዩበት አምስት አመት ውስጥ በሶስቱ ከሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ በላይ ሆነው ማጠናቀቅ ችለዋል።

ባለፈው አመት በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ ተቃርቦ የነበረው ብሬንትፎርድ በዚህ አመት ትልቅ አላማ አንግቧል።

ቡድኑ በዛሬው ጨዋታ የተደራጀ ሆኖ ሲታይ የመሐል ሜዳውን በመቆጣጠርም ሶስት ጥሩ ስራ የታየባቸው ጎሎች አስቆጥሯል።

ብሬንትፎርድ አጠቃላይ ባደረጋቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች 14 ጎል ሲያስቆጥር የተቆጠረበት ግብ 3 ብቻ ነበር።

ቡድኑ እያሳየ ካለው እንቅስቃሴ አንፃር ከቡድኑ ብዙ እንዲጠበቅ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። 

ብሬንትፎርድ ከፕርሚየር ሊጉ ክለቦች መካከል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ድንቅ ብቃታቸውን ካሳዩ ቡድኖች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች