ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ አላማችን ማለፍ ነበር ” ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ አላማችን ማለፍ ነበር ” ሮቤርቶ ማርቲኔዝ
“ አላማችን ማለፍ ነበር ” ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

“ ሮናልዶ በድንቅ የአካል ብቃት ላይ ነው ”

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ቡድኑ ለቀጣይ ጨዋታዎች ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

“ አላማችን ማለፍ ነበር “ ያሉት አሰልጣኙ “ አሁን እያንዳንዱን ነገር ማሸነፍ እንፈልጋለን ቡድኑ ለቀጣይ ጨዋታዎች ዝግጁ ነው ” ብለዋል።

አክለውም “ እያንዳንዱን ጨዋታ 3ለ0 እያሸነፈ አለም ዋንጫ ያነሳ ቡድን በታሪክ የለም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ሮናልዶን ለምን እንዳልቀየሩት የተጠየቁት ሮቤርቶ ማርቲኔዝ “ እሱ ዋና አጥቂያችን ነው ጎል ለማስቆጠር የሚሮጥልን ተጨዋች ነው “ብለዋል።

“ እሱ በጥሩ የአካል ብቃት ሁኔታ ላይ ነው ፤ የተጫዋቾቹን ቁመና በቅርበት እንከታታ እሱ ያለው ቁጥር ምርጥ መሆኑን አይተናል።“ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች