ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አርሰናል ተጨማሪ ተጨዋች ያስፈርም ይሆን ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አርሰናል ተጨማሪ ተጨዋች ያስፈርም ይሆን ?
አርሰናል ተጨማሪ ተጨዋች ያስፈርም ይሆን ?

መድፈኞቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አራት ተጨዋቾችን ለዋናው ቡድናቸው አስፈርመዋል።

አርሰናል ሁነኛ የፊት መስመር ተጨዋች ለማስፈረም ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

አሁን ባለው ሁኔታ አርሰናል ተጨዋች ማስፈረሙ እውን የሚሆንበት እድል አነስተኛ መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ክለቡ ኢላማ ያደረገው ጁሊያን አልቫሬዝ ዝውውሩ ሊጠናቀቅ ቢቃረብ አሁንም ሀሳብ አለመቀየሩ ተዘግቧል።

አርሰናል ሌሎች አማራጮችን ላይ ቢወያይም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ጊዜ ላይበቃው ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ሚኬል አርቴታ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ " ቡድኑን ለማጠናከር እየሰራን ነው እስከሚዘጋ ያንን እናደርጋለን "ብለው ነበር።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች