ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ አጃኢባ የቀረችው የአለም አትሌቲክስ መልዕክት ልኮልን ነው ” ኮማንደር ስለሺ ስህን

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ አጃኢባ የቀረችው የአለም አትሌቲክስ መልዕክት ልኮልን ነው ” ኮማንደር ስለሺ ስህን
“ አጃኢባ የቀረችው የአለም አትሌቲክስ መልዕክት ልኮልን ነው ” ኮማንደር ስለሺ ስህን

በአሜሪካ በሚካሄደው የወጣቶች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ የነበረችው አትሌት አጃኢባ አሊዬ ወደ ስፍራው አላቀናችም።

በ 400ሜ ጥሩ ውጤት ያላት አትሌት አጃይባ አሊዬ በውድድሩ ለሜዳልያ ተጠብቃ ነበር።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን አትሌቷ በምን ምክንያት እንደቀረች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኮማንደር ስለሺ ስህን በሰጡት አስተያየት “ አጃኢባ የአጭር ርቀት ሯጭ እንደመሆኗ በልዩነት ነገሮችን አመቻችተን ስናዘጋጃት ነበር ” ብለዋል።

“ ነገርግን የአለም አትሌቲክስ ህክምና ቡድን አትሌቷ እንዳትመጣ የሚል መልዕክት ስለላከ ልትቀር ችላለች “ ሲሉ ኮማንደር ስለሺ ስህን ተናግረዋል።

ሁሉም አትሌቶች የዶፒንግ እና የሆርሞን ምርመራ ማድረጋቸውን ያነሱት ስለሺ ስህን “ የህክምና መረጃው የተላከው በአትሌቶቹ ኢሜል ነው “ ብለዋል።

አትሌት አጃኢባ አሊዬ ተጨማሪ መረጃዎች እንደተላከላት እና በፌዴሬሽኑ ቢሮ ተገኝታ በዚህ ምክንያት እንደቀረች ከህክምና ቡድኑ ጋር መነጋገሯን ጨምረው ተናግረዋል።

የመረጃው ባለቤት ፋና ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች