ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ኡሊ ሁነስ በጎረቤታቸው ተከሰሱ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ኡሊ ሁነስ በጎረቤታቸው ተከሰሱ !
ኡሊ ሁነስ በጎረቤታቸው ተከሰሱ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒኩ የክብር ፕሬዝዳንት ኡሊ ሁነስ በመኖሪያ ቤት ጎረቤታቸው ተከሰዋል።

ኡሊ ሁነስ በጎረቤታቸው የቀረበባቸው ክስ ባልተፈቀደ ቦታ ሁለት ዛፎችን ተክለዋል በሚል መሆኑ ተገልጿል።

ክስ የመሰረተባቸው ጎረቤት ኡሊ ሁነስ ዛኞችን ድንበር ላይ ባልተገባ ቦታ ነው የተከሉት ያንሱልኝ ባይ ነው።

ኡሊ ሁነስ በበኩላቸው ዛፎቹን የመትከል መብት አለኝ በማለት ተከራክረዋል።

ፕሬዝዳንት ኡሊ ሁነስ ስለ ክሱ አስተያየት ተጠይቀው ከፍርዱ በፊት አስተያየት አልሰጥም ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች