ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

እንግሊዝ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
እንግሊዝ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች !
እንግሊዝ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች !

አስር ጎሎች በተቆጠሩበት የአለም ዋንጫ የሶስተኛ ደረጃ ጨዋታ እንግሊዝ ፈረንሳይን 6ለ4 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

የሶስቱን አናብስት የማሸነፊያ ግቦች ቡካዩ ሳካ 3x ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ቤሊንግሀም እና ኮንሳ አስቆጥረዋል።

ለፈረንሳይ ግቦቹን ኪሊያን ምባፔ 2x ፣ ኡስማን ዴምቤሌ እና ባርኮላ ከመረብ አሳርፈዋል።

ጁድ ቤሊንግሀም በአለም ዋንጫው ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

ቡካዮ ሳካ በአለም ዋንጫው የመጀመሪያ ሀትሪኩ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

እንግሊዝ ማሸነፏን ተከትሎ በአለም ዋንጫው ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።

ኪሊያን ምባፔ በአለም ዋንጫው 1️⃣0️⃣ ጎል በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

🇫🇷 ኪሊያን ምባፔ በምሽቱ ጨዋታ ምን አሳካ ?

- ኪሊያን ምባፔ 2️⃣2️⃣ኛ የአለም ዋንጫ ጎሉን በማስቆጠሩ የምንጊዜም የውድድሩ ግብ አግብ ሪከርድን የግሉ አድርጓል።

- በውድድሩ አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው 🇦🇷 ሊዮኔል ሜሲ 2️⃣1️⃣ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወሳል።

- ኪሊያን ምባፔ በዘንድሮ የአለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ 1️⃣0️⃣ ከፍ አድርጓል።

- ምባፔ ከ ኮከብ ግብ አግቢነቱ በተጨማሪ በ 1️⃣4️⃣ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን በማድረግ ቀዳሚው ሆኖ ይገኛል።

- ኪሊያን ምባፔ በአለም ዋንጫው በድምሩ ባደረጋቸው 2️⃣2️⃣ ጨዋታዎች ነው 2️⃣2️⃣ ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች