“ እኛ ቀይ ካርድ ነው ያሰረዝነው እንግሊዝ ግን ከዚህ የከፋ አድርጋለች ”

የአሜሪካ አለም ዋንጫ አዘጋጅ ግብረ ኃይል ሀላፊ አንድሬው ጁላኒ ዶናልድ ትራምፕ ቀይ ካርድ ማሰረዛቸውን “ ስህተትን ማረም ” ሲሉ ገልፀውታል።
ሀላፊው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልክ መደወላቸውን “ ትክክል ” ሲሉ የደገፉ ሲሆን “ እንግሊዝ ግን የከፋ አድርጋለች “ ሲሉ ወቅሰዋል።
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር የጨዋታ ሰዓት ማስቀየራቸውን የገለፁት ሀላፊው ይሄ ከእኛ የከፋ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
እንዴት የከፋ እንዳሉ ያስረዱት ሀላፊው “ በሜክሲኮ ደጋፊዎች ስለሞቱ ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት የጨዋታ ሰዓት ሊቀየር ነበር እንግሊዝ አሻፈረኝ ብላለች ” ብለዋል።
" ይሄ ነው አሳዛኝ ድርጊት " የሚሉት ሀላፊው “ የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል ይሄ ከሜዳ ላይ ድርጊት የበለጠ አሳሳቢ ነው “ ሲሉ ተደምጠዋል።
ይሁን እንጂ የእንግሊዝ እና ሜክሲኮ ጨዋታ ሰዓት ሊቀየር የነበረው በአየር ሁኔታ ምክንያት መሆኑ ሲዘገብ ነበር።
@tikvahethsport @kidusyoftahe