ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ እኛ ፈረንሳዊያን ማንንም አንፈራም “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ እኛ ፈረንሳዊያን ማንንም አንፈራም “
“ እኛ ፈረንሳዊያን ማንንም አንፈራም “

“ ጨዋታው የሚደረገው በማህበራዊ ሚዲያ አይደለም “

“ ኪሊያንም ምባፔ 100% ዝግጁ ነው “

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዋረን ዛይር ኤምሪ “ ስፔንን አሸነፍን መበቀል እንፈልጋለን “ ሲል ከጨዋታው በፊት ተናግሯል።

ዋረን ዛየር ኤምሪ “ ዝግጁ ነን “ በማለት በአውሮፓ ሻምፒዮና ላይ የደረሰባቸውን ሽንፈት መበቀል እንደሚፈልግ ገልጿል።

ተጫዋቹ አክሎም “ እኛ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ነን ማንንም አንፈራም ፣ ጨዋታው የሚደረገው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አይደለም“ ሲል ለስፔናዊያን ምላሽ ሰጥቷል።

አሰልጣኝ ዲድዬ ዴሾ በበኩላቸው ኮከባቸው ኪሊያን ምባፔ “ 100% ዝግጁ ነው “ ሲሉ በጨዋታው እንደምንመለከተው ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም የስፔን አነስተኛ ግብ ማስተናገድን ሲያነሱ “ ምክንያቱ ተጋጣሚዎቻቸው የግብ እድሎችን ለመፍጠር እና ኳስን ለመያዝ ስለተቸገሩ ነው “ ብለዋል።

ስላለፉት የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እንደማያስቡ የገለፁት አሰልጣኙ “ ምንም አይነት በቀል የለም “ ሲሉ ተናግረዋል።

ስለ ያማል የተጠየቁት ዲድዬ ዴሾ “ ከ እኔ ልጆች ጋር በአንድ ለአንድ ግንኙነት መፋለም ፓርክ ውስጥ ወክ እንደማድረግ አይደለም “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች