ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ “
“ ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ “

በወላጅ እናታቸው ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ያልነበሩት ዲድዬ ዴሾ “ ከባድ ጊዜ ነበር “ ብለዋል።

አሰልጣኙ “ ወደ ስራ ገበታዬ ተመልሻለሁ “ ሲሉ ከስዊድን ጋር ያላባቸውን ጨዋታ “ የሞት ሽረት “ በማለት ገልፀውታል።

የፈረንሳይ ተጨዋቾች ባለፈው ጨዋታ ለሀዘኑ ጥቁር ጨርቅ ለማሰር ጠይቀው ፊፋ ውድቅ አድርጎ ነበር።

ዲዲዬ ዴሾ ስለ ክስተቱ ተጠይቀው “ ብሔራዊ ቡድኑ ትልቅ ድጋፍ አሳይቶኛል ያ የሚቀይረው ነገር አይኖርም ነበር ” ብለዋል።

አክለውም “ ማድረግ ስለመቻሉ አላውቅም ነገርግን ለውጥ የለውም ተጨማሪ ነገር አያስፈልግም "ሲሉ ገልጸዋል።

የቡድኑ ተጫዋች አድርያን ራቢዮ በበኩሉ “ ጥሩ ነገር ለመስራት ተመልሶ መጥቷል ፣ በቆይታው ምቾች የሚሰጠውን ነገር ሁሉ እናደርግለታለን “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች