ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ዋልያዎቹን በነቂስ መጥታችሁ እንደምትደግፉ እምነት አለኝ “ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ዋልያዎቹን በነቂስ መጥታችሁ እንደምትደግፉ እምነት አለኝ “ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
“ ዋልያዎቹን በነቂስ መጥታችሁ እንደምትደግፉ እምነት አለኝ “ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

“ የግብ ጠባቂ እጥረት እየተፈጠረ ነው ”

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ደጋፊዎች ብሔራዊ ቡድኑን በነቂስ ወጥተው እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋልያዎቹ በሚቀጥሉት 14 ቀናት ውስጥ ከሱዳን እና ሴኔጋል ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ።

“ ብሔራዊ ቡድኑን በነቂስ መጥታችሁ እንደምትደግፉ እምነት አለኝ “ ሲሉ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስለ ግብ ጠባቂዎች ያነሱት አሰልጣኙ “ በአሁኑ ሰዓት የግብ ጠባቂዎች እጥረት እየተፈጠረ ነው ” ሲሉ አሳውቀዋል።

“ በቀጣይ በሊጉ እንኳ ከ 18 ቡድኖች 16ቱ የውጪ ናቸው “ ያሉት አሰልጣኙ “ ክለቦች በዚህ ላይ ተባብረን ብንሰራ ሲሉ ተደምጠዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ “ መላው አለም የሚጠቀመውን እኛ ለምን እንደማንጠቀም አይገባኝም “ ሲሉ ገልፀዋል።

- ከ 40 በላይ በጀርመን
- ከ 60 በላይ ከ 17-19 ዓመት የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ መጫወት እንደሚፈልጉ አስረድተዋል።

አክለውም “ ህጎች ተፈፃሚ ሲሆኑ ያሉንን ተጫዋቾች ከ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አጣምረን የተሻለ ብሔራዊ ቡድን በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል “ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ጥምር ዜግነት የማይፈቅድ በመሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በብሔራዊ ቡድኑ ማካተት አለመቻሉ ይታወቃል።

የካፍ እና ፊፋ ደንብ አንድ ተጨዋች ብሔራዊ ቡድን ለመወከል የሀገሩን ፓስፖርት ይዞ እንዲገኝ ያስገድዳል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች