ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ዘንድሮ ጫማዬን ልሰቅል እችላለሁ ” ሮናልዶ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ዘንድሮ ጫማዬን ልሰቅል እችላለሁ ” ሮናልዶ
“ ዘንድሮ ጫማዬን ልሰቅል እችላለሁ ” ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ  አመት ጫማውን ሊሰቅል እንደሚችል አስታወቀ።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአል ነስር ያለው ውል ቀጣይ ክረምት ያበቃል።

“ ይህ አመት ምናልባት የእግርኳስ የመጨረሻዬ ነው ” ያለው ሮናልዶ “ አስደናቂ አሻራዬን ትቼ መሄድ እፈልጋለሁ ” ብሏል።

ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ምን እንደሚያደርግ የተጠየቀው ሮናልዶ “ አንድ መጥቀስ አልችልም ብዙ ነገሮችን አደርጋለሁ “ ብሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ አያይዞም ጉዞዎችን ማድረግ እና አዝናኝ ነገሮችን ማድረግ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

የ 41ዓመቱ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 1000 ለማድረስ 24 ጎሎች ይቀሩታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች