የማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ሁኔታ ?

የማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ሁኔታ ?
ጋላታሳራይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ቢጠይቅም ተጨዋቹ በክለቡ ለመቀጠል ወስኗል።
ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ተጫዋቹን የመሸጥ ፍላጎት የሌለው ሲሆን ውሉን ለማደስ ንግግሩን ቀጥሏል።
በሌላ በኩል በዝውውር መስኮቱ ፈጣን ዝውውሮች የፈፀመው ማንችስተር ዩናይትድ ከዛን ጊዜ በኋላ አዲስ ተጨዋች አላስፈረመም።
ይሁን እንጂ ማንችስተር ዩናይትድ በተወሰኑ ቦታዎች መጠናከር እንደሚፈልግ በቅርብ ጨዋታዎች ታይቷል።
አሰልጣኝ ማይክል ካሪክም ይህንኑ ያረጋገጡት ሲሆን መጠናከር ያለባቸው ሁለት ወይም አንድ ቦታ አለን ብለዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የግራ መስመር ተሰላፊ ማስፈረም የመጀመሪያ ኢላማው እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም ክለቡ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ለማስፈረም እንደሚመለከት ተዘግቧል።
ሁለቱን ቦታዎች በአንድ ላይ መሸፈን ጥሩ ተጨዋች ከተገኘ በክለቡ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ተነግሯል።
በሌላ በኩል ክለቡ አጥቂ የሚያስፈርምበት እድል በጆሽዋ ዚርኪዜ መልቀቅ ጋር የተገናኘ መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe