ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የራሽፎርድ ውል ማፍረሻ ቀነ ገደብ አብቅቷል !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የራሽፎርድ ውል ማፍረሻ ቀነ ገደብ አብቅቷል !
የራሽፎርድ ውል ማፍረሻ ቀነ ገደብ አብቅቷል !

ማርከስ ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ የነበረው የ 40 ሚልዮን ፓውንድ የውል ማፍረሻ ቀነ ገደብ መጠናቀቁ ተነግሯል።

ይህም ማለት ከዚህ በኋላ ማርከስ ራሽፎርድን መግዛት የሚፈልግ ክለብ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር መደራደር ይኖርበታል።

የተጨዋቹ ውል ማፍረሻ ለክለቡ ተቀናቃኞች ሊቨርፑል እና ማንችስተር ሲቲ ቀድሞውን እንደማይሰራ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ራሽፎርድ ከክለቦቹ አሁን ከሚያገኘው የበለጠ ከፍተኛ ክፍያ ቀርቦለት ውድቅ ማድረጉን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ነገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ ከቀጠሉ ማርከስ ራሽፎርድ ከአለም ዋንጫ መልስ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሏል።

ባርሴሎና ራሽፎርድን በ 30 ሚልዮን ፓውንድ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ ቢኖራቸውም አለመፈለጋቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች