ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የስፔን የጨዋታ ብልጫ ዛሬስ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የስፔን የጨዋታ ብልጫ ዛሬስ ?
የስፔን የጨዋታ ብልጫ ዛሬስ ?

ስፔን በተከታታይ 2️⃣8️⃣ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ከተጋጣሚዎቿ የበለጠ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስዳለች።

ይህም ብራዚል ከ1966 እስከ 1974 ባሉት ጊዜያት ካደረጓቸው 1️⃣4️⃣ ጨዋታዎች በእጥፍ የሚበልጥ ሆኖ ይገኛል።

ስፔን ከ ቤልጅዬም በነበራት መርሐ ግብር :-

- 6️⃣8️⃣ % የኳስ ቁጥጥር ብልጫ
- 1️⃣7️⃣ የግብ ሙከራ
- 1️⃣3️⃣ የግብ እድሎች ፈጥረው ነበር።

ኳስን ተቆጣጥሮ መጫወት የስፔን ብሔራዊ ቡድን የጨዋታ መንገድ ሆኖ ለረጅም አመታት ታይቷል።

በዚህም “ ወርቃማው ትውልድ “ ከ 2008 -2012 ባሉት አመታት አለም ዋንጫን ጨምሮ ሶስት አህጉራዊ ስኬቶችን ተጎናፅፏል።

ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ዋናውን የስፔን ቡድን ከመያዛቸው አስቀድሞ በተለያዩ የብሔራዊ ቡድኑ የእድሜ ቡድኖች ላይ በሀላፊነት አገልግለዋል።

ይህም የሀገሪቱ የጨዋታ መንገድ የሆነው ኳስን ተቆጣጥሮ ተጋጣሚን የማሸነፍ ታክቲክ በቀላሉ ለመተግበር ረድቷቸዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች