ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የአርሰናል ተጨዋቾች ጉዳት ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የአርሰናል ተጨዋቾች ጉዳት ሁኔታ ?
የአርሰናል ተጨዋቾች ጉዳት ሁኔታ ?

የአርሰናሉ ተከላካይ ጁሪየን ቲምበር ወደ ልምምድ መመለሱን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

“ ቲምበር በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው  ያለው ” ያሉት አርቴታ “ በቼልሲ ጨዋታ ስለመሰለፉ ነገ አይተነው እንወስናለን ” ብለዋል።

ብሩኖ ጉማሬሽ በአስቶን ቪላ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንደተሰማው የገለፁት አርቴታ “ ለነገ ልምምድ ዝግጁ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ” ሲሉ ገልጸዋል።

ሙስኬራ ግን ባለፈው ጨዋታ ለጥንቃቄ ተቀይሮ መውጣቱን በመግለፅ “ እንዴት እንዳለ ማየት አለብን " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች