ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የአርሰናል የዝውውር ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የአርሰናል የዝውውር ሁኔታ ?
የአርሰናል የዝውውር ሁኔታ ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሁንም ብሩኖ ጉማሬሽን ለማስፈረም እየተከታተለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኒውካስል በያዘው አቋም የሚቀጥል ከሆነ ግን መድፈኞቹ ሌሎች አማራጮች መመልከት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

አርሰናል በተመጣጣኝ ዋጋ ሊመለከተው የሚችለው ተጨዋች የሮማው ማኑ ኮኔ መሆኑ ተዘግቧል።

በሌላ በኩል አርሰናል በሮጀርስ ዝውውር ምትክ ትልቅ ዝውውር ሊፈፅም እንደሚችል ተነግሯል።

አርሰናል ቡድኑን ወደ ትልቅ ደረጃ የሚወስድ ኮከብ ተጨዋች እየፈለገ መሆኑ ተዘግቧል።

ጁሊያን አልፋሬዝ አሁንም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለማስፈረም የሚያልሙት ተጨዋች ሆኖ ይገኛል።

አርሰናል እድሉን የሚያገኝ ከሆነ ጁሊያን አልቫሬዝን ለማስፈረም እንደሚጠቀምበት ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች