ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነን ማንንም አንፈራም “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነን ማንንም አንፈራም “
“ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነን ማንንም አንፈራም “

“ ዛሬ የምንገባው ወደ ጦርነት ነው “

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ላሚን ያማል “ በእግር ኳስ ህይወቴ ወሳኙን ጨዋታ ዛሬ አደርጋለሁ “ ሲል ከፈረንሳይ የምሽቱ ጨዋታ በፊት ተናግሯል።

“ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነን “ የሚለው ያማል “ ምንም አይነት ፍርሀት በየትኛውም ጨዋታ አይሰማንም “ ሲል ይናገራል ።

ላሚን ያማል “ ጫና የለብኝም “ ሲል “ በምችለው መንገድ ሁሉ ለሀገሬ ያለኝን ነገር በሙሉ እሰጣለሁ “ ብሏል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ በበኩላቸው “ እግር ኳስ ቀላል ጨዋታ ነው “ ሲሉ “ የጨዋታ መንገዱን በሚገባ የሚተገብር ቡድን አሸንፎ ይወጣል “ ብለዋል።


በአለም ዋንጫው ለፍፃሜ ለማለፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን ፣ ዛሬ የምንገባው ወደ ጦርነት ነው

“ አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች