ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኮሎምቢያ ተጨዋች የግድያ ዛቻ ደረሰበት !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኮሎምቢያ ተጨዋች የግድያ ዛቻ ደረሰበት !
የኮሎምቢያ ተጨዋች የግድያ ዛቻ ደረሰበት !

በስዊዘርላንድ ጨዋታ ያለቀለት የግብ እድል ያመከነው የኮሎምቢያ ተጨዋች ጃሚንተን ካምፓዝ የግድያ ማስፈራሪያ ደርሶታል።

ከጨዋታው በኋላ በተጨዋቹ እና በቤተሰቡ ላይ የግድያ ማስፈራሪያዎች እንደደረሱ ተዘግቧል።

የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ድርጊቱን በማውገዝ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ በይፋ ጥያቄ አቅርቧል።

ከዚህ በፊት በኮሎምቢያ እግርኳስ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ተመሳሳይ ድርጊት እንደነበር ይታወቃል።

በ 1994 አለም ዋንጫ ኮሎምቢያ ከምድብ ስትሰናበት በርካታ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የግድያ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር።

በወቅቱ የውድድሩ አዘጋጅ በተመሳሳይ አሜሪካ የነበረች ሲሆን የቡድኑ ተከላካይ አንድሬሰ ኢስኮባር በራሱ ላይ ጎል አስቆጥሮ ነበር።

የ 27ዓመቱ ተከላካይ አንድሬስ ኢስኮባር ወደ ሀገሩ ሲመለስ ከሀያ ቀናት በኋላ በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች