ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዋልያዎቹ ተጫዋች ለኩዌት ክለብ ፈረመ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዋልያዎቹ ተጫዋች ለኩዌት ክለብ ፈረመ !
የዋልያዎቹ ተጫዋች ለኩዌት ክለብ ፈረመ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌት ሊግ ማምራቱ ለማወቅ ተችሏል።

በሳውዲው ክለብ አል አረቢ ጥሩ ጊዜን በግሉ ያሳለፈው ጋቶች ፓኖም ለኩዌቱ አል ፋሂሊ ክለብ ፊርማውን ማኖር ችሏል።

ጋቶች ፓኖም በክለቡ ለአንድ አመት ለመቆየት ለአል ፋሂሊ ስፖርት ክለብ ፊርማውን አኑሯል።

ጋቶች ፓኖም ከሳምንታት በኃላ ወደ ግብፅ በማቅናት በቅድመ ውድድት ዝግጅት ቡድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

ጋቶች ፓኖም ከሀገራችን ሊግ አልፎ :-

በሩሲያ
ኢራቅ
ግብፅ እና
ሳውዲ አረቢያ ሊጎች ላይ ባለፉት አመታት ተጫውቶ አሳልፏል።

“ ጭልፊቶቹ “ የሚል መጠርያ ያለው ክለቡ አስር ክለቦች በሚሳተፉበት የሀገሪቱ ሊግ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 6️⃣ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች