ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዋልያዎቹ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዋልያዎቹ ዝግጅት ምን ይመስላል ?
የዋልያዎቹ ዝግጅት ምን ይመስላል ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊቱ ለሚጠብቀው የ 2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተሞች ላይ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።

ቡድኑ በዝግጅት ወቅቱ ሶስት የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርግ

- ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

- ከ ኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዎ ቡድን ( 2X )

- ሀዋሳ ከተማ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን አድርጓል።

ቡድኑ ዝግጅቱን አጠናቆ በነገው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታውን በሚያደርግበት ደቡብ ሱዳን ከተማ ጁባ ጉዞውን ያደርጋል። 

ዋልያዎቹ የፊታችን አርብ ከሱዳን 🇸🇩 ጋር እንዲሁም በቀጣይ ሳምንት ዕሮብ ከ ሴኔጋል 🇸🇳 ጋር በባህርዳር ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አፍሪካ ዋንጫ ለመግባት የሚደረግ ውድድር መሆኑን ያነሱት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “ የምንወዳደረው ለማሸነፍ ነው ፣ ይሄ የታዳጊ ቡድን አይደለም ” ብለዋል።

“ ስምምነቴ ቡድኑን ለማሳለፍ ነው ከላሳለፍኩኝ ሌላ አዲስ አሰልጣኝ ይመጣል።” ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

“ ከሚዲያ ጋር ግንኙነት የለኝም ያለኝ የስራ እና ሙያዊ ግንኙነት ነው “ ያሉት አሰልጣኙ “ የተሰጠኝ የሚልዮኞች አደራ ነው ” ብለዋል።

“ በኔ እና በሚዲያ መካከል መርህ መኖር አለበት ፣ ፌዴሬሽኑ የካፍ መመርያን ተከትሏል ልምምድ 15 ደቂቃ ፈቅዷል።” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

ስለ ተጨዋች አመራረጥ መስፈርታቸው የተነሳላቸው አሰልጣኙ “ ተጫዋች የምመረጥው በወቅታዊ አቋም ብቻ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ አቅም ካለን ልናሸንፍ እንችላለን ከእኛ የተሻለ ካለ ልንሸነፍ እንችላለን ዋናው አላማችን ግን ማሸነፍ ነው ” ሲሉ ስለ ቀጣይ ጨዋታዎች ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች