ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዛሬ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዛሬ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?
የዛሬ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

የአምስት ጊዜ የአለም ሻምፒዮኗ ብራዚል 🇧🇷 ከ ጃፓን 🇯🇵 ጋር በምታደርገው ጨዋታ የዕለቱ መርሐ ግብር ምሽት 2️⃣:0️⃣0️⃣ ላይ መካሄዱን ይጀምራል።

አለም ዋንጫውን ካሸነፉ 2️⃣4️⃣ዓመታት ያስቆጠረችው ብራዚል ዘንድሮም ውድድሩን ለማሸነፍ ቅድመ ግምት አግኝታለች።

የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በአለም ዋንጫው አሸንፋ የማታውቀው ጃፓን በበኩሏ በጫና ውስጥም ሆኗ ለብራዚል ቀላል እንደማትሆን ይጠበቃል።

የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ጀርመን 🇩🇪 ዝቅተኛ ግምት ከተሰጣት ፓራጓይ 🇵🇾 ጋር ከምሽቱ 5️⃣:3️⃣0️⃣ ሲል መርሐ ግብሯን ታካሂዳለች።

በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብርም ኔዘርላንድ 🇳🇱 ከ ሞሮኮ 🇲🇦 ጋር ከሌሊቱ 1️⃣0️⃣:0️⃣0️⃣ በሚያደርጉት ጨዋታ ፍፃሜውን ያገኛል።

በሁለቱ መርሐ ግብር የሞሮኮዎቹ :-

- ሶፍያን አምራባት
- ናስር ማዝራዊ
- አናስ ሳላህዲን ትውልዳቸው ኔዘርላንድ ቢሆንም ሞሮኮን ወክለው ለመጫወት ምርጫቸው አድርገዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች