ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ያለኝን ሰጥቻለሁ በንፁህ ህሊና ነው የምሄደው ”  - ሮናልዶ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ያለኝን ሰጥቻለሁ በንፁህ ህሊና ነው የምሄደው ”  - ሮናልዶ
“ ያለኝን ሰጥቻለሁ በንፁህ ህሊና ነው የምሄደው ”  - ሮናልዶ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከቡድኑ ስንብት በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሮናልዶ በሰጠው ቃል ማዘኑን ገልፆ “ ነገርግን ንፁህ ህሊና ይዤ እሄዳለሁ ምክንያቱም የነበረኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ ” ብሏል።

“ ነገ አዲህ ቀን ነው ህይወት ይቀጥላል ” ያለው ሮናልዶ “ የቻልኩትን ስላደረኩ በእያንዳንዱ ቀን በንፁህ ህሊና እነቃለሁ "ሲል ገልጿል።

የአለም ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታዬ ነው ያለው ሮናልዶ “ በፖርቹጋል ግን የመጨረሻ ጨዋታዬ አይመስለኝም ገና አልወሰንኩም “ብሏል።

በፖርቹጋል የመጀመሪያ ትልቅ ዋንጫ ማሸነፉ ትልቅ ትርጉም እንዳለው የገለፀው ሮናልዶ “ ለእኔ ዋጋው እንደ አለም ዋንጫ ነው ”ሲል ገልፆታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች