ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ጉማሬሽን የሸጥነው ሪከርድ በሆነ ዋጋ ነው “

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ጉማሬሽን የሸጥነው ሪከርድ በሆነ ዋጋ ነው “
“ ጉማሬሽን የሸጥነው ሪከርድ በሆነ ዋጋ ነው “

“ አርሰናል ካሰበው በላይ ከፍሏል ”

ኒውካስል ዩናይትድ በዚህ ክረምት ብሩኖ ጉማሬሽን የመሸጥ እቅድ እንዳልነበረው የክለቡ ሀላፊዎች ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ሀላፊዎቹ ኒውካስል ተጫዋቹን በጥሩ ዋጋ ሸጦታል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የኒውካስል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሮስ ዊልሰን “ ክፍያው በእሱ እድሜ ላለ ተጨዋች የአለም ሪከርድ ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም “ እሱን በዚህ ክረምት መሸጥ እቅዳችን አልነበረም ነገርግን እዚህ መሆን ካልፈለገ ብቸኛው አማራጭ ነው “ ሲሉ ተደምጠዋል።

የክለቡ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ሆፕኪንሰን በበኩላቸው “ አርሰናል መክፈል አስቦ ከነበረው በላይ ከፍሏል “ ብለዋል።

“ ገንዘቡ ለእኛ ከመጠን በላይ ነው “ ያሉት ሆፕኪንሰን በገበያው ዋጋ ከለካነው ከአለም ከፍተኛው ነው ብለዋል።

የ 28ዓመቱ አማካይ ብሩኖ ጉማሬሽ በ 7️⃣5️⃣ ሚልዮን ፓውንድ አርሰናልን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች