ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#TeamEthiopia 🇪🇹

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#TeamEthiopia 🇪🇹
#TeamEthiopia 🇪🇹

በነገው ዕለት ወሳኝ ጨዋታ ያለበት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል።

ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከዛምቢያ አቻው ጋር ያደርጋል።

የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በዛምቢያ የ 2ለ1 አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረገው የመጨረሻ ልምምድ :-

- የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ
- ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን
- የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሪት ብዙዓየሁ ጀምበሩ እና
- የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ እና ዛምቢያ የመልስ ጨዋታ ነገ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል።

የጨዋታው የስታዲየም መግቢያ በነፃ ሲሆን ስፖርት አፍቃሪው ተገኝቶ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያበረታታ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች