#WorldAthleticsU20

#WorldAthleticsU20
የአለም አትሌቲክስ ከ 20ዓመት በታች ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት በአሜሪካ ኦሬገን መካሄድ ይጀመራል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች ትሳተፋለች።
ኢትዮጵያ በውድድሩ በ 5000ሜ ፣ 3000ሜ ፣ 1500ሜ ፣ 800ሜ እና እርምጃ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ትካፈላለች።
እንዲሁም በ3000ሜ መሰናክል በሴቶች ብቻ እንደምትካፈል ይጠበቃል።
በዛሬው የውድድሩ መክፈቻ ዕለት የ 5000ሜ ፍፃሜ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ይደረጋሉ።
በሴቶች 5000ሜ ፍፃሜ ዩጋንዳዊቷ አትሌት ቻሪቲ ቼሮፕ የኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብርቱ ተፎካካሪ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ ርቀት ኢትዮጵያዊቷ ሽቶ ጉሚ ትልቅ ግምት ስታገኝ አትሌት እመቤት ጥላሁን ሌላኛዋ አይን የተጣለባት ኢትዮጵያዊት አትሌት ነች።
በወንዶች 5000ሜ ፍፃሜ ኢትዮጵያ በአትሌት ዳምጠው ከበደ እና ማማሩ ጓዴ የምትወከል ይሆናል።
የዛሬ መርሐ ግብር ?
ምሽት 4:35 - 800ሜ ወንዶች ማጣሪያ
ምሽት 5:15 - 800ሜ ሴቶች ማጣሪያ
ንጋት 11:53 - 5000ሜ ሴቶች ፍፃሜ
ጠዋት 12:20 - 5000ሜ ወንዶች ፍፃሜ
@tikvahethsport @kidusyoftahe