ላለፋት ስድስት ወራት ታግዶ የቆየውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪሎቹ የዘገባ ፈቃድ ተደሰ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ላለፋት ስድስት ወራት ታግዶ የቆየውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪሎቹ የዘገባ ፈቃድ ተደሰ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ከዓለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ኒክ ታተር እና የአፍሪካ ኤዲተር ሲልቪያ አሎይሲ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት፣ " ሮይተርስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባለፉት ሰባት ወራት ካሰራጫቸው የሚዲያ ይዘቶች መካከል የተወሰኑት የአገራችን ህጎች፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያዊ ስነምግባር ያልተከተሉ ነበሩ " ሲሉ የባለስልጣኑ የሚዲያ ሞኒተሪንግ ዉጤቶችን መሠረት በማድረግ ገልጸውላቸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሮይተርስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያሰራጫቸው ዘገባዎችን ይዘት የተሰራጩበትን ቀንና ርእሰ ጉዳዮቾን በመጥቀስ ፦
- የሚዛናዊነት፣
- የትክክለኝነት፣
- የተአማኒነትና የተጨባጭነት ችግር የተስተዋለባቸውና ወደ አንድ ወገን ያደሉ እንደነበሩ አስረድተዋል።
ይህም የአራችንን ህግ፣ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁን እንዲሁም የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር ጥሰት የተስተዋላባቸው እንደነበሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።
በውይይቱ፣ የሮይተርስ ሃላፊዎች አስፈላጊዉን እርማትና ማስተካከያ የዜና ተቋሙ እንደሚያደርግ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የሮይተርስ ሃላፊዎች የዜና ወኪሉ ገለልተኛ ሚዲያ መሆኑን ገልጸው ፤ ዘገባዎችን ሚዛናዊ በሆነ፣ በበቂ መረጃ ተመስርቶ፣ ከአድልዎ በጸዳ መልኩ ለመሥራት ጥብቅ የኤዲቶሪያል መመሪያዎችን እንደሚከተል አስታውቀዋል።
እንዲሁም አልፎ አልፎ ለሚፈጠሩ ስህተቶችም ይቅርታ ጠይቀው ማስተካከያ እንደሚሰጡ አስገንዝበዋል።
ሮይተርስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ክብር እንዳለው፤ ሀገሪቱ ባላት የህዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ግዝፈት ልክ ዓለም አቀፍ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ማግኘት አለባት ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል።
ሮይተርስ የኢትዮጵያን ሕግ አክብሮ እንደሚሠራ፣ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ እሴቶች ሽፋን መስጠት እንደሚፈልግም አመልክተዋል።
ጋዜጠኞቹም የሙያ ሥነ-ምግባርን አክብረው መሥራት እንዳለባቸው እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እንደሚረዱና አቋሟንም እንደሚያከብሩም አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ማጠናቀቂያ ላይም ከህግና የሙያ ስነምግባር ጥሰት ጋር ተያይዞ ለጊዜው ታግዶ የቆየው የሮይተርስ የኢትዮጵያ የዜና ወኪሎች የዘገባ ፈቃድ እንዲታደስላቸው በባለሥልጣኑ ተደርጓል።
ምንጭ፦ https://www.facebook.com/share/1DF8WxTaDJ/
ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia