ስኬት ባንክ ጠቅላላ የሀብት መጠኑን በ51% በማሳደግ 29 ቢሊዮን ብር አደረሰ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ስኬት ባንክ ጠቅላላ የሀብት መጠኑን በ51% በማሳደግ 29 ቢሊዮን ብር አደረሰ።
ስኬት ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2026/27 የትኩረት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ነሐሴ 02 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ በቀረበው አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደተገለጸው፣ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 10.3 ቢሊዮን ብር ማድረስ የቻለ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉንም ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር አሳድጓል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ባከናወነው የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ 14.7 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። በዚህም በበጀት ዓመቱ 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት 1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ የቻለ ሲሆን አጠቃላይ የሀብት መጠኑንም ወደ 29 ቢሊዮን ብር አድርሷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ የበጀት ዓመቱ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል። አያይዘውም በ2026/27 የበጀት ዓመት የባንኩን ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማሳደግ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለደንበኞች የሚሰጡ የአገልግሎት አማራጮችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን በመንደፍ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም፣ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ስኬት ባንክ የስኬትዎ መሠረት!