" በውላችን መሰረት ክፍያው አልተከፈለንም። ... ከፍተኛ የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ ወድቀናል " - ባለሙያዎች
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በውላችን መሰረት ክፍያው አልተከፈለንም። ... ከፍተኛ የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ ወድቀናል " - ባለሙያዎች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፌሴላዊ የመስክ አሠልጣኞች፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎችና የቆጠራ አስተባባሪዎች ቦርዱ በገባው ውል መሠረት የአገልግሎት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው እየገለጹ ነው።
ባለሙያዎቹ፣ የተጣለባቸውን ሙያዊና የዜግነት ኃላፊነት መወጣታቸውን፣ ነገር ግን ከምርጫ ቦርድ ጋር በገቡት ውል መሠረት ሊከፈላቸው የሚገባ የአገልግሎትና የጉዞ አበል ክፍያ እንዳልተከፈላቸው አሳውቀዋል።
በውሉ መሠረት የተሰጧቸውን ሥራዎች ሙሉ በሙሉ በሰዓቱ ማጠናቀቃቸውን ግን ክፍያቸው በሰዓቱ እንዳልተከፈላቸው ከቦርዱ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ባደረጓቸው ውይይቶችና በጽሑፍ ማሳሰቢያ ጭምር ቢያቀርቡም ምላሽ ሆነ መፍትሔ እንዳላገኙ አስረድተዋል፡፡
በዋናነት ቦርዱ በገባው ውል መሠረት ክፍያዎቹን በወቅቱ የመፈጸም ግዴታውን ባለመወጣቱ በባለሙያዎቹ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ጫና መፈጠሩን፣ በወቅቱ በነበረው አስቸጋሪና ተለዋዋጭ የሥራ ሁኔታ ምክንያት የተፈቀደውንና በውሉ የሠፈረውን የጉዞና የዕለት የውሎ አበል እስካሁን እንዳልተከፈለና የውሉን መንፈስ የሚቃረን ድርጊት መፈጸሙ አብራርተዋል፡፡
የቦርዱ ኃላፊዎች ለመብታችን ግዴለሽነትን እያሳዩ ነው በማለትም ከሰዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን መለሰ ?
ቦርዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ማብራሪያ ይህን ብሏል።
" ለምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ለመስጠት መሥፈርቱን አሟልተው የተመለመሉና ሥልጠና የወሰዱ ባለሙያዎች ወደ ሥልጠና ከመሰማራታቸው በፊት፦
- የአሠልጣኞች ሥልጠና በሚሰጥበት ጊዜ መገኘት፣
- በሥልጠናው ወቅት ሰዓት መቆጣጠሪያ በአግባቡ መፈረም፣
- ሥልጠናውን ሲያጠናቅቁ የሥራ ውል መፈረምና ሥልጠና በሚሰጡበት ወቅት የሰዓት መቆጣጠሪያ በየቀኑ መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
ሥልጠናውን ሰጥተው ሲያጠናቅቁ ኃላፊነታቸውን በውሉ መሠረት መፈጸማቸው ከተለየና የማረጋገጥ ሥራ ከተከናወነ በኋላ ክፍያ ይፈጸማል።
ቦርዱ ምርጫ ለማስፈጸም የተመደበለትን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የመቆጣጠር ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት፣ ሥልጠና ከወሰዱና ውል ከገቡ በኋላ ወደ ተመደቡበት ሥልጠና ማዕከል በመሄድ በውላቸው መሠረት ሥልጠና የማይሰጡ ባለሙያዎች በመኖራቸው ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት የማጥራት ሥራ ይከናወናል።
በአንዳንድ አካባቢዎች አሠልጣኞች ከተመደቡበባቸው የሥልጠና ማዕከላት በተጨማሪ በሌሎች ማዕከላት ተዘዋውረው ሥልጠና የሚሰጡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፤ ክፍያው ለትክክለኛው ባለሙያ በአግባቡ መከፈል እንዲቻል ተጨማሪ የማጥራት ሥራ ይከናወናል።
ሁሉም መሥፈርቶች ተሟልተው መቅረባቸውንና የክፍያው ጥያቄ በድጋሚ የቀረበ ባለመሆኑ፣ የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ ከተከናወነ በኋላ ክፍያው ይፈጸማል።
በተጨማሪ ምርጫው የተካሄደው የበጀት መዝጊያው በተቃረበበት ወቅት ነው። በመደበኛ በጀትና በምርጫ በጀት የተፈጸሙ በርካታ የአገልግሎት ግዥዎች ክፍያ በተመሳሳይ ጊዜ እየተፈጸሙ ስለነበሩና ውስን ክፍያዎች ተፈጽመው ከመጠናቀቃቸው በፊት፣ የቦርዱ ካዝና ውስጥ የነበረው በጀት ሙሉ በሙሉ ክፍያ ተፈጽሞበት ተጠናቋል።
በተመሳሳይ ጊዜ የበጀት ዓመቱ በመጠናቀቁም ተጨማሪ በጀት እንዲለቀቅልንና የቀሩትን ውስን ክፍያዎች ከፍለን ማጠናቀቅ እንድንችል ጥያቄ አቅርበን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን። "
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia