ታካሚዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት ጭምር ያስከተሉ የህክምና ስህተት አቤቱታዎች መቅረባቸውንና የሚቀርቡ አቤቱታዎች እየጨመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለ…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ታካሚዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት ጭምር ያስከተሉ የህክምና ስህተት አቤቱታዎች መቅረባቸውንና የሚቀርቡ አቤቱታዎች እየጨመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ገለጸ።
የባለስልጣኑ የህግ፣ የጤና ባለሙያዎችና ሥነምግባር ክትትል ዳይሬክር አቶ መትከል ገብረመድህን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ከህክምና ስህተት ጋር በተያያዘ 42 አቤቱታዎች ቀርበዋል።
የቀረቡት አቤቱታዎች ምን የተመለከቱ ናቸው? በእነዚህ አቤቱታዎች በህክምና ስህተት የሞቱ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የሚመለከቱ አሉ? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ዳይሬክተሩ፣ "አዎን። እሱማ አለ። የአካል ጉዳትም አለ፤ ሞትም አለ" ብለዋል።
"ግን እንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሚዲያ ላይ ሲወጣ ባለሙያዎች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም" ብለው፣ የሟችና ጉዳተኞችን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
የህክምና ስህተት ተፈጸመ በሚል የሚያቀረቡ አቤቱታ እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ነው? መንስኤው ምንድን ነው? ስንላቸው፣ "በተለያዩ መንገዶች በደንብ እየሰራን ስለሆነ ህብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግንዛቤው እየዳበረ መጥቷል። ግንዛቤ እየዳበረ በመምጣቱ የሚቀርበው የቅሬታ መጠንም ከፍ እያለ መጥቷል" ብለዋል።
"የቅሬታ መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው" ያሉን ሲሆን፣ "ይህ ማለት የህክምና ስህተት ጨምሮ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ ያ በጥናት ነው የሚረጋገጠው" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የሚቀርቡ አቤቱታዎች ሲጨምሩ በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ የመጨመር እድሉ ሰፊ መሆኑንም ገልጸዋል።
አቶ መትከል 42 አቤቱታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ፣ "31 የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎችን ተጠያቂ አድርገናል። በማጣራት ሂደት ብዙ ባለሙያዎች ናቸው የሚሳተፉት፤ ከበርካታ ባለሙያዎች መካከል ነው 31 ባለሙያዎችን ተጠያቂ ያደረግነው" ሲሉ ነግረውናል።
ዘንድሮ 42 ሰዎች ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ምን እንደሆኑ ስንጠይቃቸው፥ የሞት፣ የአካል ጉዳት አቤቱታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
- በጨቅላ ህፃናት፣
- በነፍሰጡሮች፣
- በጥርስ ህክምና
- በዓይን ህክምና
- በውስጥ ደዌ በሽታዎች
- በወሊድ እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች መሆኑንም አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፥ ጤና ባለሙያዎች የህክምና ስህተት ለመፈጸሙ ምክንያት የሚሉት ምንድን ነው? ሲል የጠየቃቸው አቶ መትከል፣ "የተለያዩ ምክንያቶች ሊያቀርቡ ይችላሉ። የሚያቀርቡት ምክንያት ግን ትክክለኛ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የህክምና ግብዓት እጥረት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ "ትኩረት አለመስጠት"፣ "የሙያ ማነስ"፣ "የእውቀት እና ክህሎት ማነስ" ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ፣ "ከ42 አቤቱታዎች ውስጥ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኛ የተባሉትን፦
- 3 ሚድዋይፈሪ፣
- 9 ዶክተሮች፣
- 14 ነርሶች፣
- 3 ጤና መኮንን፣
- 1 አንስቴቲስት፣
- 1 የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ በድምሩ 31 ጤና ባለሙያዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተወስኖባቸዋል" ሲል አስታውቋል።
30 ባለሙያዎች ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ከሁለት ወር የሚደርስ የሙያ ፈቃድ እገዳ እንደተጣለባቸው፣ አንድ ባለሙያ ላይ ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia