አሜሪካ ከ6 ሳምንታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እሁድ ምሽት ኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ማገርሸቱን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

አሜሪካ ከ6 ሳምንታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እሁድ ምሽት ኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ማገርሸቱን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።
ባለፈው ሳምንት ቅናሽ ሲመዘገብበት የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከአሜሪካ ጥቃት በኋላ የሁለት በመቶ ገደማ ጭማሪ ታይቶበታል።
የነዳጅ ዋጋ መለኪያ ተደርጎ የሚቆጠረው ብሬንት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ የ1.77 ዶላር ጭማሪ ታይቶበት በ89.87 ዶላር እየተሸጠ ነው።
አሜሪካ ከሐምሌ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚታወቅ ደረጃ በፈጸመችው የትናንቱ ጥቃት ላራክ በተባለው የኢራን ደሴት የሚገኙ ሁለት ማስወንጨፊያዎችን መምታቷን አስታውቃለች።
ይህንን ተከትሎም ኢራን በዮርዳኖስ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገልጻለች።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።
ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia