" እስከ ሐምሌ 25 ድረስ የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" እስከ ሐምሌ 25 ድረስ የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የደረሳችሁ ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያቸውን ፈጽሙ። መልዕክት ያልደረሳችሁ ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳቸው ግብር ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ድረስ መክፈል ትችላላችሁ " - ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የግብር ዘመን በመዲናዋ ከተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ 456 ሺህ 433 የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች 9.2 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቋል።
ቢሮው እንደገለጸው፣ አብዛኞቹ የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በኦንላይን ስርዓት መክፈላቸውን ሲጠቅስ፣ የተቀሩትም በክፍያ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
በክፍያ ጊዜ ሰሌዳው መሠረት፣ እስከ ሐምሌ 25 ድረስ የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የደረሳቸው ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ተጠይቀዋል። መልዕክት ያልደረሳቸው ወይም ከሐምሌ 25 በኋላ የደረሳቸው ግብር ከፋዮች ደግሞ ያለቅጣት እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መክፈል እንደሚችሉ ተገልጿል።
ቢሮው በተጨማሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በግብር አሰባሰብ ስርዓት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጿል። እንዲሁም የደረጃ "ለ" ነጋዴዎች የሚከፍሉት ግብር ከተቀጣሪ ሠራተኞች ያነሰ መሆኑን ጠቅሶ፣ ይህም አነስተኛ ንግዶችን ለማበረታታት የተወሰደ አሠራር መሆኑን አስረድቷል።
በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ የአዲስ አበባ 502.27 ቢሊየን ብር በጀት ማጽደቋን ጠቅሶ፣ ከዚህ ውስጥ 380 ቢሊየን ብር ገቢ በገቢዎች ቢሮ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቋል።
በሌላ በኩል፣ በደረጃ "ለ" ግብር አከፋፈል ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች የአፈታት ስርዓት መዘርጋቱን ቢሮው ገልጿል። በስልክ የተላከው የዓመታዊ ግብር መጠን በቅድመ ታክስ የተከፈለውን ገንዘብ ተቀናሽ አድርጎ የተሰላ መሆኑን ጠቅሶ፣ በግብር መጠኑ ላይ ቅሬታ ያላቸው ግብር ከፋዮች በተዘረጋው የቅሬታ አፈታት ስርዓት ተጠቅመው ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።
(የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ)