" ከልጆቻችን ጉሮሮ ተቀንሶ የተወሰደብን እህል ይመለስ፣ በሌሊት ጭነው የወሰዱት አካላት በሕግ ይጠየቁልን " - የአንካ ድጉና ቀበሌ ነዋሪዎች
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ከልጆቻችን ጉሮሮ ተቀንሶ የተወሰደብን እህል ይመለስ፣ በሌሊት ጭነው የወሰዱት አካላት በሕግ ይጠየቁልን " - የአንካ ድጉና ቀበሌ ነዋሪዎች
👉 " የደረሰን አቤቱታ የለም " - የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ድጉና ፋንጎ ወረዳ፣ አንካ ድጉና ቀበሌ በሚገኘው አንካ ብሳሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የተዘጋጁ ልዩ ልዩ የምግብ ቁሳቁሶች ከትምህርት ቤቱ ተጭነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ሽማግሌዎች፣ የቀበሌው ስራ አስኪያጅ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
አካባቢው በድርቅ መመታቱን ተከተሎ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ከቀረበው ድጋፍ ውስጥ ፦
- ሩዝ፣
- ዘይት፣
- ቦለቄ፣
- ቂንጬ፣
- ስንዴና ጨው ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ገደማ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርና በቀበሌው ሊቀመንበር አስተባባሪነት በሞተር ሳይክሎች ተጭኖ መወሰዱ ተናግረዋል።
የአንካ ድጉና ቀበሌ ሥራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ኮይሻ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " የምግብ ቁሳቁሱ ከትምህርት ቤቱ መወሰዱን አረጋግጫለሁ " ብለዋክ።
ድርጊቱን በተመለከተ የቀበሌውን ሊቀመንበር በጠየቁበት ወቅት "በፈለኩበት ሰዓት ገብቼ ማውጣት እችላለሁ" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ለሚመለከታቸው የወረዳው አመራሮች ሪፖርት መደረጉን የጠቀሱ ሲሆን ጉዳዩ በህግ እንዲታይ የጠየቁ አንዳንድ የስራ ሃላፊዎች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉንና " ድርጊቱን ፈጽመዋል " የተባሉት አካላት አሁንም በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የቀበሌው ሽማግሌ አቶ ሳሙኤል አልጋ በበኩላቸው፣ የሞተር ድምጽ ሰምተው ወደ ትምህርት ቤቱ ማምራታቸውን ጠቅሰው፤ በትምህርት ቤቱ ጥበቃ ላይ የነበረው ግለሰብ በቀበሌው ሊቀመንበር አቶ አሰፋ ኡሹላ " የሚጫኑ ነገሮች አሉ ላስጭናቸው ነው፣ አንተ ዝም ብለህ ተኛ " ተብሎ ማስፈራሪያ ደርሶት እህሉ መጫኑን እንደነገራቸው ገልጸዋል።
አያይዘውም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እና የቀበሌው ሊቀመንበር ንብረቱን በሞተር ጭነው ሲወስዱ ማየታቸውን ጠቅሰው፣ ማህበረሰቡ ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባሉት አካላት በደረሰበት ጫና እና "እንታሰራለን" በሚል ፍርሃት ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ከመውሰድ መቆጠቡን ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ " ከልጆቻችን ጉሮሮ ተቀንሶ የተሸጠው እህል ዋጋው ተተምኖ ገንዘቡ ለትምህርት ቤቱ ገቢ እንዲደረግና እህሉንም የሸጡት አካላት በህግ ይጠየቁ " ብለዋል።
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም አንካ ማዘጋጃና አንካ ድጉና ቀበሌን የሚያገናኝ ድልድይ በመበላሸቱ ለጥገና ሥራ የተገዛው 20 ኩንታል ሲሚንቶና ሌሎች ቁሳቁሶች ለነጋዴ ተሸጠው ድልድዩ ሳያልቅ መቅረቱን አክለው አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በእህሉ ጉዳይ ስማቸው የተነሳውን የአንካ ድጉና ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ አሰፋ ኡሹላን አነጋግሯል።
የቀረበባቸውን አቤቱታ ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።
ሊቀመንበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ " በእኔ ላይ የቀረበው አቤቱታ በሙሉ ውሸት ነው፤ እኔ እንደዚህ አይነት ሰው አይደለሁም፣ ምንም የወሰድኩት ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።
የድጉና ፋንጎ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት፣ ፖሊስ እና አስተዳደር በበኩላቸው እስከ አሁን ወደ እነሱ የደረሰ ምንም ዓይነት ቅሬታ ወይም ጥቆማ እንደሌለ በመግለጽ ድርጊቱን አስተባብለዋል።
የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ተመስገን ታምራት፣ " የደረሰኝ አቤቱታ የለም " ያሉ ሲሆን ጉዳዩ በትምህርት ጽሕፈት ቤቱ ተጣርቶ ሪፖርት ከተደረገ ማንኛውም አካል ከሕግ በላይ ስለማይሆን እንደሚጠየቅ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል፣ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የትምህርት ቤቱ መምህር የወረዳው አስተዳደር፣ ፖሊስ እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ስለ ጉዳዩ እንደሚያውቁና መበዝበሩን ለመሸፈን እየሞከሩ እንደሆነ ገልጿል።
አቤቱታ አቅራቢዎቹ ለወረዳው አስተዳደር የተበዘበዘውን ንብረት አስመልክቶ አቤቱታ ያቀረቡበትን ማመልከቻ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia