ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ከቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ቀጥሎ ትልቁ ሁለተኛው ቴርሚናል የተገነባው ባህርዳር ከተማ ነው " -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ከቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ቀጥሎ ትልቁ ሁለተኛው ቴርሚናል የተገነባው ባህርዳር ከተማ ነው " -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
" ከቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ቀጥሎ ትልቁ ሁለተኛው ቴርሚናል የተገነባው ባህርዳር ከተማ ነው " -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አዲሱን ቴርሚናል መርቀዋል።

በዚህም ወቅት ባሰሙት ንግግር የከተማዋን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ የገቢ አቅምን ማሳደግ እና ሰላምን ማስፈን መሠረታዊ መስፈርቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ልማት በቀጣይነት ባለመሰራቱ ባህርዳርን ማየት በሚገባን ልክ ሳናይ ብንቆይም አሁን ላይ መልካም ጅማሮዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ስለከተማዋ ገቢ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ " በኢትዮጵያ ውስጥ ከቦሌ ቀጥሎ ትልቁ ተርሚናል አለ ብንልም፣ ትልቁ ድልድይ አለ ብንልም፣ ትላልቅ ሪዞርቶች ተገነቡ ብንልም፣ ስታድየም እያለቀ ነው ብንልም፤ ዛሬ ባህርዳር ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከተሞች ገቢዋ ሰባተኛ ደረጃ ነው " ብለዋል።

አክለውም፥ " ይህ ገቢ ካልተሻሻለ በስተቀረ ከንቲባ ጎሹ ከተማን መቀየር አይችልም ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን የሰራውን ጭምር ሜይንቴን ማድረግ አይችልም " ሲሉ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወነውን የሪፎርም ሥራ ያደነቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፍርድ ቤቱ በቨርቹዋል ችሎቶችን ለመከታተልና ቅሬታዎችን ለማስተናገድ የዘረጋው አሠራር ለፍትህ መረጋገጥ አስደናቂ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

ስለ ሰላም ሲያነሱም፥ "ቀኙ ግራውን መቆንጠጥ ካልቻለ፣ ቀኙ ግራውን ማሳረፍ ካልቻለ ያየናቸው ተስፋዎችና ሙከራዎች ሊበላሹ ይችላሉ" ብለዋል።

አክለውም "ሰላም ውድ ስጦታ፣ ጊዜ ትልቅ ሀብት፣ ስራ ትልቅ ጸጋ፣ ትብብርና በጋራ መቆም ከማንኛውም ጊዜ በላይ የሚያስፈልግበት ዘመን ነው። ካልተግባባን ደግሞ እንደጨዋ በንግግር እንጨካጨቅ፤ ጊዜ ግን እንዳያልፍን እንጠንቀቅ" ሲሉ አሳስበዋል።

ስለ ክልሉ አመራር ሲገልጹም፥ "ባለፉት 30 ዓመታት እንደዚህ እንደዛሬው ዘመን የአማራ ክልልም ሆነ ባህርዳር እራሱን በራሱ በተሟላ መንገድ የሚያስተዳድርበት ዘመን አልነበረም።

ፕሬዝዳንታችን ከነሙሉ ክብራቸው እና ህግ በሰጣቸው ስልጣን ጋር ያሻቸውን መወሰን የሚችሉ የታመኑ፣ የተወደዱ፣ የተከበሩ፣ የሚሰሩና የሚያሰሩ ፕረዚዳንት ናቸው" ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች